ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከብራዚል ፕሬዝደንት ሉዊዝ ኢናቺዮ ሉላ ደ ሲልቫ ጋር መወያየታቸዉን ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ከ17ኛው የብሪክስ ጉባኤ አስቀድሞ ከብራዚል ፕሬዝደንት ሉዊዝ ኢናቺዮ ሉላ ደ ሲልቫ ጋር ተገናኝተን በሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል ብለዋል፡፡
የዛሬው ውይይታችን በቅርብ እያደገ የመጣውን የሁለቱ ሀገሮቻችንን ግንኙነት የበለጠ በማጠናከር ረገድ አንድ ርምጃ ወደፊት የወሰደን ሆኗል።
በተለያዩ ዘርፎች የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትስስሮቻችንን የበለጠ ለማጠናከር ተስማምተናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡