በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት አርብ እለት የተከሰተውን የጎርፍ አደጋ ተከትሎ የሟቾች ቁጥር በትንሹ 81 የደረሰ ሲሆን ሌሎች 41 ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም።
የአደጋው ሰለባዎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ሲሆን የሟቾች ቁጥር አሁንም ሊጨምር እንደሚችል ባለስልጣናትን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል።
እየቀጠለ ያለው ከባድ የአየር ሁኔታ ለነፍስ አድን ስራው እንቅፋት እንዳይሆን ስጋት አስከትሏል።
በሊያት ካሳሁን