ኢትዮጵያ በብሪክስ ጉባኤ ውጤታማ ጊዜ እያሳለፈች መሆኑን የኮሙኒኬሽን አገልገሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለፁ

You are currently viewing ኢትዮጵያ በብሪክስ ጉባኤ ውጤታማ ጊዜ እያሳለፈች መሆኑን የኮሙኒኬሽን አገልገሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለፁ

AMN- ሰኔ 30/2017

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ልዑካቸው በብራዚል እየተካሄደ በሚገኘው የመሪዎች ጉባኤ ላይ ውጤታማ ጊዜ እያሳለፈ እንደሚገኝ የኮሙኒኬሽን አገልገሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ልዑኩ ወደ ሪዩ ዲ ጀኔሮ ያቀናው በብሪክስ አባል ሀገራት መሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ እና የሁለትዮሽ ግንኙነትን ይበልጥ ለማጠናከር ታስቢ አድርጎ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በተለይም ሠላም እና ደህንነት አስመልክቶ ዓለም የሁሉንም ድምጽ የምትሰማበት ሁኔታ እንዲኖር መሪዎቹ ትኩረት ሰጥተው መወያየታቸውንም የኮሙኒኬሽን አገልገሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

የደቡብ እስያና ላቲን አሜሪካ ድምፅ የማይሰማበት፣ ዓለም ከግጭት ወደ ግጭት የሚያመራበትና ኢ-ተገማች እና አዳዲስ ስጋቶች እየተፈጠሩ መምጣታቸውንም ጉባኤው በአፅንዖት ተመልክቷል፡፡

በመላዉ አለም የሚገኙ ድምጾች እኩል እንዲደመጡ ተልዕኮ የተሰጣቸው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሥር የሚገኙ እንደ ፀጥታው ምክር ቤት ያሉት ተቋማት ሪፎርም ሊያደርጉ እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡

በመድረኩ እየተሳተፉ የሚገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማዕከል በማድረግ ዓለም አቃፊ ልትሆን እንደሚገባና በተለይም የአፍሪካ ድምፅም በሁሉም የዓለም ተቋማት በእኩል ከመደመጥም አልፎ ተሳትፎዋም እንዲረጋገጥ አፅዖት ሰጥተው ንግግር ማድረጋቸውን አብራርተዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review