የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር አመራርና ሠራተኞች የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄዱ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር አመራርና ሠራተኞች የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄዱ

AMN ሃምሌ 05/2017 ዓ.ም

“በመትከል ማሰራራት” በሚል መሪ ሃሳብ በተከናወነው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ የባለስልጣን መ/ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ የጉለሌ፤ የየካ፣ የለሚኩራና የቦሌ አመራሮችና የደንብ አስከባሪ ኦፊሰሮች ተገኝተዋል፡፡

በዘንድሮው ዓመት በተለያዩ ቦታዎች ከ10 ሺህ በላይ ችግኞችን ለመትከል የሚያስችል ቦታ በመረከብ ችግኞችን የመትከልና በዘላቂነትም የመንከባከብ ሥራ እንደሚከናወን የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ተናግረዋል።

በ90 ቀን የበጎ ተግባር ስራ የአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስ፣ ደም መለገስ ተግባራትም እንደሚከናወን አክለዋል።

በፍቃዱ ምስጋናው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review