የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ በዛሬው የአሶሳ ጉበኝታችን አዲሰ አበባ ላይ ከዓመት ዓመት ባህል እየሆነ የመጣውን የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት፣ የምገባ ማዕከል ማቋቋም፣ የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም አካል የሆነው የህፃናት መጫወቻ ቦታዎች ግንባታን እና የፅዱ ኢትዮጵያ ሥራዎችን አሶሳ ከተማ ላይ አስጀምረናል ብለዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትራችን የስራ አቅጣጫ መሰረት የአዲስ አበባን አሮጌ ገጽታ እና የድህነት ታሪክ ለመቀየር በመልሶ ማልማት እና በኮሪደር ልማት ስራ ከህዝብ ውይይት እስከ ትግበራ 24/7 በመስራት እንዲሁም ህዝባችንን የልማቱ ባለቤት በማድረግ ያመጣነውን ተጨባጭ ወጤት እና ተሞክሮዎቻችንን አካፍለናል ሲሉም አክለዋል።
ወደ ክልሎች እየተስፋፋ ያለውን እና በአሶሳ ከተማ እየተሰራ ያለዉን የኮሪደር ልማት የክልሉ ፕሬዝዳንት አሻድሊ ሃሰን አስጎብኝተውናል ሲሉም ነው የገለጹት።