በበጀት ዓመቱ ከ1.3 ቢሊየን ዶላር በላይ የሚገመቱ ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን መተካት መቻሉን የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንደስትሪ ቢሮ አስታወቀ

You are currently viewing በበጀት ዓመቱ ከ1.3 ቢሊየን ዶላር በላይ የሚገመቱ ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን መተካት መቻሉን የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንደስትሪ ቢሮ አስታወቀ

AMN – ሐምሌ 6/2017 ዓ.ም

በበጀት ዓመቱ ከ1.3 ቢሊየን ዶላር በላይ የሚገመቱ ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት መተካት መቻሉን የኦሮሚያ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንደስትሪ ቢሮ አስታወቀ።

በኦሮሚያ ክልል በ2017 በጀት ዓመት በኢንቨስትመንት ዘርፍ አበረታች ስራዎች መከናወናቸውን የክልሉ አንቨስትመንትና ኢንደስትሪ ቢሮ ቢኃላፊ አቶ አህመድ ኢድሪስ ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱ የዝግጅት ምእራፍ፣ የክልሉን የኢንቨስትመንት አቅምን አስመልክቶ በተሰራው ሰፊ የማስተዋወቅ ስራ በርካታ የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ ኢንቨስተሮችን መሳብ ተችሏል ብለዋል።

ከ300 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያላቸውን ከ20 ሺህ በላይ ኢንቨስተሮችን መቀበል መቻሉን የገለጹት ኃላፊው፣ ከእነዚህ ውስጥ ከ12 ሺህ በላይ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ወደ ስራ ማስገባት የተቻለ መሆኑንም ገልጸዋል።

በተላያዩ ምክንያት ወደ ስራ ሳይገቡ የቆዩ 3 ሺህ 600 በለይ ነባር የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ወደ ምርት ማስገባት መቻሉንም ተናግረዋል።

እንደ ክልል ተኪ ምርቶችን የሚያመርቱ ኢንደስትሪዎችን በልዩ ሁኔታ በመደገፍ በተሰራው ስራ 1.3 ቢሊየን ዶላር የሚገመቱ ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት የተቻለ ሲሆን፣ በአንጻሩ ከ1 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ከኤክስፖርት ምርት ተገኝቷል ብለዋል።

በዘርፉ ከ375 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ እና ጊዚያዊ የስራ እድል ተፈጥሯል ያሉት አቶ አህመድ፣ የኢንቨስትመንት የቅበላ አቅምን ለማሳደግ የሰራተኞችን የመፈጸም አቅም ከማሳደግ ባለፈ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስራ መሰራቱንም ተናግረዋል።

በተያዘው 2018 በጀት ዓመት የነበሩ ክፍተቶችን በማረም፣ በክልሉ ያለውን የኢንቨስትመንት አቅም አሟጦ ለመጠቀም በጊዜ የለኝም መንፈስ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

በሄኖክ ዘነበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review