የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ ቴስላ ኩባንያ ከፍተኛ ዋጋ የተቆረጠላትን ዋይ ሞዴል መኪና በህንድ ሙምባይ አስተዋውቋል፡፡
አዲሷ ዋይ ሞደል መኪና በ70 ሺህ ዶላር ለገበያ መቅረቧ ማክሰኞ እለት ይፋ ተደርጓል፡፡
በህንድ ከውጭ በሚገቡ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለውን ከፍተኛ ታሪፍ ተከትሎ የመሸጫ ዋጋዋ ከሌሎች ገበያዎች አንፃር ከፍተኛ ሊሆን ችሏል፡፡
በርግጥ የቴስላ ሥራ አስፈፃሚና እና የዓለማችን ቁጥር አንድ ቱጃሩ ኤለን መስክ ከዋጋው መወደድ ጋር ተያይዞ ብዙ ትችት አስተናግዷል፡፡
አራት በመቶ ያህሉን የአሜሪካን የመኪና ገበያ ሽያጭ በመሸፈን 3ኛው የዓለማችን ትልቁ የመኪና ግብይት ማዕከል የሆነችው ህንድ በበርካታ የአሜሪካ መኪና አምራች ኩባንያዎች ዐይን ውስጥ ገብታለች፡፡
በህንድ ሰፊ ግብይት ያላቸው ታታ ሞተርስ እና ማሂንድራን በብዙ እጥፍ ይበልጣል የተባለለት አዲሱ የቴስላ ምርት ዋይ ሞዴል መኪና ከቅንጡዎቹ የጀርመን ቢ ኤም ደብሊው ፣ መርሴዲስ ቤንዝ እና ከደቡብ ኮሪያው ኪያ ከተሰኙ መኪናዎች ጋር የሚወዳደር ነው ተብሏል፡፡
በህንድ ገበያ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ዘመናዊው ዋይ ሞዴል ማክሰኞ እለት በሙምባይ የማሳያ ማዕከሉ የተዋወቀ ሲሆን በአሁኑ ሰዓትም ትዕዛዞችን እየተቀበለ እንደሚገኝ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
በማሬ ቃጦ