ከንቲባ አዳነች አቤቤ አብረን አቅደን፣ አብረን ሰርተን፣ አብረን ውጤት አምጥተናል ሲሉ ገለጹ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ አብረን አቅደን፣ አብረን ሰርተን፣ አብረን ውጤት አምጥተናል ሲሉ ገለጹ

AMN ሃምሌ 13/2017

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት ባለፉት ቀናት ስናካሂድ የነበረው የከተማችን የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት አጠናቅቀናል ብለዋል።

በግምገማችንም የተመዘገቡ አበረታች ውጤቶችን በማላቅ እና የተለዩ ድክመቶችን በማረም በቀጣይ የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ተግባብተናል ።

ከተማችን በሁሉም ዘርፍ ለነዋሪዎቿ ምቹ ፣ ሀገራዊና አህጉራዊ ብሎም አለምአ ቀፋዊ ሚናዋን በብቃት የምትወጣ ፤ ስሟና ግብሯ የተናበበ ከተማ እንድትሆን የጀመርነዉን ልማት በጥራት፣ በስፋትና በፍጥነት አጠናክረን እንደምንቀጥል ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን ሲሉ ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review