በመዲናዋ በ2017 በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም ያመጡ ተቋማት ሽልማቱ ስራቸውን አብልጠው እንዲተጉ ስንቅ እንደሚሆናቸው ገለፁ

You are currently viewing በመዲናዋ በ2017 በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም ያመጡ ተቋማት ሽልማቱ ስራቸውን አብልጠው እንዲተጉ ስንቅ እንደሚሆናቸው ገለፁ

‎AMN ሐምሌ 15 /2017 ዓ.ም

‎የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ተቋማትና ክፍለ ከተሞች እውቅና ሰጥቷል፡፡

‎ለውጤት የበቁት ሰራተኛውና አመራሩ በጥሩ መንፈስ ተዋህደው በመስራታቸው የመጣ ውጤት እንደሆነ የአዲስ አበባ ከተማ የዲይዛንናግንባታ ስራዎች ሀላፊ ኢንጂነር አያልነሽ ሀብተማርያም ተናግረዋል ።

‎መሸለማቸው የቀጣይ ራዕያቸውን ከፍ እስኪል እንዲሰሩ የሚያነሳሳ እንደሆነ ገልፀው፣ከህብረተሰቡና ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅተዉ መስራታቸዉ ለውጤት እንዳበቃቸው አስረድተዋል።

‎የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሊድያ ግርማ በበኩላቸው፣ በፀጥታ ጉዳይ የውጤታማነት ትልቁ ምክንያት ከህዝብ ጋር መስራታቸን ነው ብለዋል።

‎የተሰጣቸዉ እዉቅና ስራቸውን በላቀ ሁኔታ እንዲፈጽሙ ስንቅ እንደሚሆንላቸዉም ወ/ሮ ሊድያ አመላክተዋል።

‎የአዲስ አበባ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ እናት አለም መለሰ ሽልማቱ የበለጠ እንድንሰራ አቅም ፈጥሮልናል ብለዋል፡፡

‎የለሚ ኩራ ክፍለከተማ ዋናስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ በበኩላቸዉ በወጣቶች፣ሴቶችና በተለይም አርሶ አደሮች ተጠቃሚነት ላይ በትኩረት በመስራታቸው የተገኘ ውጤት ነው ብለዋል፡፡

‎ሌሎችም ለዚህ ሽልማት የበቁ ተቋማት ክፍለከተሞች እና ወረዳዎች ውጤታቸውን አስጠብቀው ለመጓዝና አፈፃፀማቸውን ከነበሩበት ከፍ ለማድረግ እንደሚሰሩ አመላክተዋል።

‎በሔለን ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review