ያለፉት 6 ዓመታት ገድል በነገዉ እለትም እንደሚደገም ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

You are currently viewing ያለፉት 6 ዓመታት ገድል በነገዉ እለትም እንደሚደገም ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

AMN- ሐምሌ 23/2017 ዓ.ም

ያለፉት 6 ዓመታት ገድል በነገዉ እለትም ይደገማል! ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ያለፉት 6 ዓመታት ገድል በነገዉ እለትም ይደገማል! መላው የከተማችን ነዋሪዎች ፆታ፣ ዕድሜ ፣ ብሔር፣ ኃይማኖት፣ የኑሮ ደረጃ ሳይለያቸው ነገ ከማለዳ 12 ሰዓት ጀምሮ ኢትዮዽያ በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል የያዘችዉን እቅድ ለማሳካት፣ በአራቱም አቅጣጫ ድርሻችን በነቂስ እንነሳለን ብለዋል።

አዲስ አበባ በዕለቱ ዳግም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል አንድነታችንን ፣ ቁርጠኝነታችንን እና ፅናታችንን የምናሳይበት እለት ይሆናል ሲሉም አክለዋል።

ከንቲባዋ አያይዘውም ዉብ፣ አረንጓዴ፣ ጤናማ መዲና እንፈጥራለን! ነው ያሉት፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review