ከንቲባ አዳነች አቤቤ የዘንድሮውን የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አስጀመሩ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ የዘንድሮውን የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አስጀመሩ

AMN ሃምሌ 24/2017

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የዘንድሮውን የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አስጀመሩ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት የዘንድሮውን የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በታላቅ ድምቀት በይፋ አስጀምረናል ብለዋል፡፡

ከሀይማኖት አባቶች፣ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ የጤና ባለሞያዎች፣ የፀጥታ አካላት፣ ወጣቶችና ሴቶች እንዲሁም ከተለያዩ የሙያ ማህበረሰቦች ጋር በመሆን በኮሪደር ልማት ጠረኗ እና መልኳ ተቀይሮ ባማረችውና ውበት በተጎናጸፈችው አዲስ አበባ በግንፍሌ ወንዝ ዳርቻ ችግኝ ተክለናል።

በሁሉም የከተማችን አካባቢዎች በተዘጋጁ 271 ቦታዎች መላው የከተማችን ነዋሪዎች በከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜት በነቂስ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ። ማለዳ ላይ በጀመርነው መንፈስ ቀጥለን በእቅድ የያዝነዉን ግብ እንደምናሳካ እርግጠኛ ነኝ ሲሉ ገልጸዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review