ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ማለዳ የዘንድሮውን የአረንጓዴዐሻራ የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አስጀምረናል ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በጂማ ከተማ አስጀምረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለሰባተኛው ዓመት ግባችን:- ሰባት መቶ ሚሊዮን ችግኞች ነው። በጋራ እናሳካው! ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡