ችግኝ ከመትከል ባለፈ በየጊዜው እንክብካቤ ማድረግ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ ገለፁ

You are currently viewing ችግኝ ከመትከል ባለፈ በየጊዜው እንክብካቤ ማድረግ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ ገለፁ

AMN- ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የችግኝ ተከላ እየተካሄደ ይገኛል።

ከሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች የተውጣጡ በአንድ ጀምበር 700 ሚሊየን ችግኞች የመትከል እቅድን ለማሳካት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በችግኝ ተከላ መርሀ ግብሩ የተገኙት የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ፣ ችግኞችን ከመትከል ባለፈ በየጊዜው እንክብካቤ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ በበኩላቸው፣ በክፍለ ከተማው በ13 ቦታዎች በሰፊ ንቅናቄ ችግኝ የመትከል ተግባር እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ለነገ ትውልድ ለምለምና ከብክለት የፀዳች ሀገር ለማውረስ ችግኝን መትከልና መንከባከብ ይገባል ሲሉ በችግኝ ተከላው እየተሳተፉ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ተናግረዋል።

በንጉሱ በቃሉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review