የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ኢትዮጰያ ያሰበችውንና ያስቀመጠችውን ግብ ማሳካት እንደምትችል ማሳያ እንደሆነ የግብርና ሚንስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለፁ።
ባለፈው ዓመት 600 ሚሊየን ችግኞች በአንድ ጀንበር ለመትከል ታቅዶ 650 ሚሊየን ችግኞች መተከላቸውን ተናግረዋል።
በዘንድሮ ዓመት 700 ሚሊየን ችግኞችን በዛሬው ዕለት እንደሚተከሉ እና የሚተከሉትም በጂኦግራፊካል ቦታቸው የተለዩና አይነቶቹም እንደየአከባቢው መለየታቸውን ገልፀዋል።
በእያንዳንዱ ኢትዮጰያዊ የሚተከለው ችግኞች ከግዜያዊ ማስተባበርያ በቀላሉ መከታተል እንደሚቻልም ተናግረዋል።