ኢትዮጲያ በ2023 በአፍሪካ ደረጃ የብልፅግና ተምሳሌት ተብላ እንድትጠራ የሚያደርጉ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ተናግረዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት ሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ታችኛው በደኔ ቀበሌ የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ተጀምሯል።
የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፣ ለሰባት ተከታታይ ዓመት የተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ሀገራዊ የለውጥ ሂደትን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
ከተስፋ ብርሃን ወደ ተጨባጭ ተስፋ ለመሸጋገር የሚያስችል ስራ እየተሰራ መሆኑንም አንስተዋል።
ኢትዮጲያ በ2023 በአፍሪካ ደረጃ የብልፅግና ተምሳሌት ተብላ እንድትጠራ የሚያደርጉ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ የምታስመዘግባቸው ሁሉን አቀፍ ብልፅግና የአረጓዴ አሻራ ያለው ሚና ጉልህ መሆኑን አንስተው፣ ማህበረሰቡ እያደረገ ያለው በጎ ተግባር ማስቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።
ከተረጂነት ወደ ምርታማነትና በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር መንግስት የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና ለማሳደግ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት እያከናወነ መሆኑን አንስተዋል።
ባለፉት ስድስት ዓመታት በአረንጓዴ ልማት ሥራ ዘርፈ ብዙ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ለውጦች ማምጣት መቻሉን ጠቅሰዋል