በአንድ ጀንበር 700 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል መርሀ-ግብር በጅማ ያስጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ አሁን ባለው አካሄድ ከእቅዳችን በላይ እናሳካለን ሲሉ ገልፀዋል፡፡
አሁን ባለው መረጃ እስከ 500 ሚሊየን ችግኞች እንደተተከሉ የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሕብረተሰቡ አሁንም ተረባርቦ ችግኞችን እንዲተክል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ቀድመው የተከሉ እንዲደግሙ ያልተከሉ ደግሞ ወጥተው እንዲተክሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡