የኢትዮጵያ ማንሰራራት ጉዞ በባቡር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስም ዕውን መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ማንሰራራት ጉዞ በባቡር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስም ዕውን መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ
  • Post category:ልማት

AMN – ሐምሌ 26/2017 ዓ.ም‎

የኢትዮጵያ ማንሰራራት ጉዞ በባቡር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስም ዕውን መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገልጸዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልክዕክት፣ የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ስራ ከጀመረ130ኛ ዓመቱን ዛሬ አክብረናል ብለዋል፡፡

በዓድዋ የድል መንፈስ የተወለደው ይህ የባቡር አገልግሎት መስመር ከብረት የተሠራ ማጓጓዣ ብቻ አይደለም – የኢትዮጵያን የመምራት፣ የመፍጠር እና ራሷን ለዓለም የመግለጥ ፍላጎቷ ማሳያም ጭምር እንጂ ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ።

ባቡራችን አንድ ለእናቱ ሆኖ የቀረው በታሪካችን የጀመርነውን አለማጠናቀቅ እና ያለማስቀጠል ችግር ሰለባ በመሆኑ ነው። ከለውጡ ወዲህ ጀምሮ ያለመጨረስ ስብራትን ለማስወገድ “ከጀመርን ሳንጨርስ አናርፍም” በሚል መንፈስ እየተጋን ድሎችን እያስመዘገብን እንገኛለን።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒትሩ አክለውም፣ የሀገር ዕዳ ሆኖ የቆየው የኢትዮ- ጂቡቲ ባቡር በለውጡ ዓመታት በተሰጠው ትኩረት ወደ ምንዳ በመሸጋገር ላይ ይገኛል፤ የሀገር ገቢና ወጪ ንግድ ዋነኛ አንቀሳቃሽ ሆኗል። ይህ አዲስ ምዕራፍ ነው፤ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ጉዞ በባቡር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስም ዕውን ሆኗል ብለዋል፡፡

ቅድመ አያቶቻችን የዘመናዊነትን ፈር በመከተልም በአፍሪካ ቀዳሚ የባቡር መስመርን እውን አድርገዋል። አሁን ተራው የኛ ነው – ማለም፣ መገንባት፣ የጀመርነውን መጨረስ። ማሳበብ ሳይሆን መፈጸም። ታሪክ ማውራት ብቻ ሳይሆን ታሪክ መሥራታችንን መቀጠል ይገባል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ በግልጽ ራዕይ፣ በአንድነታችን እና በባቡር መሠረተልማት መስፋፋት እውን ይሆን ዘንድ መትጋት አለብን። የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር የለውጥ መሪዎችና ሙያተኞች የተጣለባችሁን አደራ በአግባቡ እየተወጣችሁ በመሆኑ በኤፌዲሪ መንግስት እና በራሴ ስም ምስጋና አቀርባለሁ ብለለዋል አቶ ተመስገን፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review