የባህር በር የሌላቸውን ሀገራት ተሳትፎ የሚገድበው የንግድ ስርዓት መሻሻል እንዳለበት የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ገለጹ፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሶስተኛውን ወደብ የሌላቸው ታዳጊ ሀገራት ጉባዔ በቱርክሜኒስታን አዋዛ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የባህር በር የሌላቸውን ሀገራት ተሳትፎ የሚገድበው ኢ-ፍትሃዊ የዓለም የንግድ ስርዓት መሻሻል እንዳለበት ገልጸዋል፡፡
የባህር በር አልባ መሆን የሀገራትን የንግድ እንቅስቃሴ ገደብ ሊበይን አይገባም ያሉት ዋና ጸሀፊው፥ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ለከፍተኛ የትራንስፖርት ወጪ እንዲዳረጉና በዓለም የንግድ ስርዓት በአግባቡ እንዳይሳተፉ እያደረጉ ያሉ ገደቦች እንዲነሱ አሳስበዋል፡፡
መረጃዎች እንደሚያሳዩት በዓለም ላይ 44 የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት የሚገኙ ሲሆን ከነዚህ መካከል 32ቱ ታዳጊ ሀገራት ናቸው።
በብርሃኑ ወርቅነህ