አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የ2017 በጀት አመት የስራ አፈፃፀም ግምገማና የ2018 በጀት አመት ዕቅድ ዉይይት እያካሄደ ነዉ

You are currently viewing አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የ2017 በጀት አመት የስራ አፈፃፀም ግምገማና የ2018 በጀት አመት ዕቅድ ዉይይት እያካሄደ ነዉ

‎AMN ነሀሴ 1/2017 ዓ.ም

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የ2017 በጀት አመት የስራ አፈፃፀም ግምገማና የ2018 በጀት አመት ዕቅድ ዉይይት እያካሄደ ነዉ።

ኤ ኤም ኤን በ2017 በጀት አመት በተለያዩ ዘርፎችና የስራ መስኮች ለማከናወን ካቀዳቸዉ ተግባራት መካከል አብዛኞቹን በመፈጸም በከተማ ደረጃ ልዩ ተሸላሚ መሆኑ በመርሃ ግብሩ ላይ በቀረበዉ ሪፖርት ተጠቅሷል።

‎የትዉልድ ድምጽ የሆነዉ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ከተሠጠዉ ተልዕኮ አንጻር ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ በመሆን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችን ከማገልገል አልፎ ሃገራዊ ተልዕኮዎችን በብቃት በመፈጸም የተሻለ ስራ ማከናወኑ በአፈጻጸም ሪፖርቱ ተነስቷል።

ተቋሙ መረጃዎችን ለህዝቡ ተደራሽ በሚያደርግባቸዉ የተለያዩ ቋንቋዎችና የሚዲያ አማራጮች በAMN ቴሌቪዥን: በAMN PLUS: በFM 96.3 : በአዲስ ልሳን ጋዜጣና በዲጂታል ሚዲያዉ ዘርፍ ህዝብና መንግስትን ከማቀራረብ: የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ ከማስቻል: የኮሪደር ልማትና የወንዝ ዳርቻ ልማት እዉን እንዲሆኑ ከማድረግ አንፃር ከፍተኛ ስራዎችን ማከናወኑ በቀረበው ሪፖርት ተመላክቷል።

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በትምህርትና ትዉልድ ግንባታ: በሠላምና ጸጥታ: በከተማ ግብርናና ስራ ዕድል ፈጠራ: የኑሮ ጫናን ከማቃለል: በአገልግሎት አሰጣጥና በመሠል የስራ መስኮች የተለያዩ ይዘቶችን በዜና: በቀጥታ ስርጭት: በፕሮግራምና ዶክመንተሪዎች ለህዝቡ ተደራሽ ማድረጉን አንስተዋል።

በመዝናኛዉ ዘርፍም አዳዲስ ይዘቶችንና አቀራረቦችን በመቅረጽ መዲናዋን የሚመጥን ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተጠቅሷል።

ተቋሙ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመታጠቅ ‎ሃገራዊና አለም አቀፋዊ ጉዳዮችን በመዳሰስና አጀንዳ በመፍጠር ጭምር ተመራጭና ቀዳሚ የመረጃ በመሆን ላይ የሚገኝ መሆኑም ተመላክቷል።

‎በሄለን ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review