የብራዚሉ ፍሉሚኔንስ ግብ ጠባቂ ፋቢዮ ዴቪሰን ሎፔዝ በኮፓ ሱዳአሜሪካ ጨዋታ ላይ ተሰልፎ በእግር ኳስ ዘመኑ አንድ ሺ 391ኛ ጨዋታውን ማድረጉን ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል፡፡
ከፈረንጆቹ 1997 ጀምሮ የፕሮፌሽናል ጨዋታውን እያደረገ የሚገኘው የ44 ዓመቱ ሎፔዝ ከፍሉሚኔንስ ባሻገር፣ ለአትሌቲኮ ፓራኔስ ፣ ለቫስኮ ደጋማ እና ለክሩዚሮ ተጫውቷል፡፡ ከነዚህ መካከል 976 ጨታዎችን ያደገው ለክሩዜሮ ነው፡፡
አንጋፋው ግብ ጠባቂ ትናንት ለፍሉሚኔንስ 235ኛ ጨዋታውን አድርጓል፡፡ የዓለም ክብረ ወሰኖችን የሚመዘግበው ጊነስ መጽሐፍ ፤ ፒተር ሺልተን አንድ ሺ 390 ጨዋታዎችን በማድረግ ሪ ክብረወሰን መያዙን ያስታውሳል፡፡
ለብራዚል ብሄራዊ ቡድን አንድም ጨዋታ አድርጎ የማያውቀው ፋቢዮ ግን ለተለያዩ ክለቦች አንድ ሺ 391 ጨዋታዎች በማድረጉ ክብረወሰኑን መረከቡ ተነግሯል፡፡
በታምራት አበራ