በከፍተኛ የሰዉነት ክብደት ምክንያት አስር እጥፍ ገንዘብ እንዲከፍል የተጠየዉ እስረኛ

You are currently viewing በከፍተኛ የሰዉነት ክብደት ምክንያት አስር እጥፍ ገንዘብ እንዲከፍል የተጠየዉ እስረኛ

AMN – ነሐሴ 16/2017 ዓ.ም

ከፍተኛ የሰውነት ክብደት ያለው እስረኛ ከተለመደው ክፍያ በተለየ መልኩ አስር እጥፍ ገንዘብ እንዲከፍል ተጠይቋል፡፡

289 ኪሎ ግራም የሰውነት ክብደት ያለው ኦስትሪያዊ ወጣት፣ ከሌሎች እስረኞች በተለየ መልኩ ከፍተኛ ተጨማሪ ገንዘብ እንዲከፍል መጠየቁን ኦዲቲ ሴንትራል በዘገባው አስነብቧል፡፡

የ29 አመቱ ወጣት ወደ እስር ቤት የወረደው ፖሊስ በመኖሪያ ቤቱ ድንገት ባደረገው ፍተሻ 45 ኪሎ ካናቢስ፣ ሁለት ኪሎ ኮኬይን፣ ሁለት ኪሎ የሚጠጋ አምፌታሚን እና ከ2ሺ በላይ የደስታ ታብሌቶች በቤቱ ውስጥ በመገኘታቸው ምክንያት ነው፡፡

ወጣቱ ወዲያው በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋለ ተወስዶ በገባበት እስር ቤት ውስጥ በክብደቱ ምክንያት አልጋ እንደሰበረ እና ወደ ሌላ እስር ቤት እንደተዘዋወረም መረጃው ጠቁሟል፡፡

በተዘዋወረበት እስር ቤት ውስጥ የወጣቱን የሰውነት ክብደት መሸከም የሚችል በጣም ጠንካራ አልጋ እንዳለ እና ከእስር ቤቱ ውጭ ለ24 ሰዓት ልዩ እንክብካቤ የሚያደርጉለት ነርሶች መኖራቸውም ተዘግቧል፡፡

ወጣቱ ከፍተኛ ውጪ እንዲከፍል የተጠየቀበት ምክንያትም ከሌሎች እስረኞች በተለየ መልኩ የሚደረጉለት እንክብካቤዎች እንደሆኑ በዘገባው ተመላክቷል፡፡

ሆኖም ግን ይህ ከፍተኛ የሰውነት ክብደት ያለው ኦስትሪያዊ ወጣት ከወትሮው በተለየ መልኩ ተጨማሪ ከፍተኛ ገንዘብ እንዲከፍል መጠየቁ አግባብ አይደለም የሚል ቅሬታ እንዳስነሳም ነው ኦዲቲ ሴንትራል በዘገባው ያመላከተው፡፡

በአስማረ መኮንን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review