አርሰናል ሊድስ ዩናይትድን በሰፊ የግብ ልዩነት በማሸነፍ የሊጉ መሪ ሆነ

You are currently viewing አርሰናል ሊድስ ዩናይትድን በሰፊ የግብ ልዩነት በማሸነፍ የሊጉ መሪ ሆነ

AMN – ነሃሴ 17/2017 ዓ.ም

የሁለተኛ ሳምንት የሊግ መርሃግብሩን በኤምሬትስ ያደረገው አርሰናል ሊድስ ዩናይትድን 5ለ0 አሸንፏል።

ቪክቶር ዮኬሬሽ ሁለት ግቦችን በጨዋታ እና በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።በተመሳሳይ ኔዘርላንዳዊ ተከላካይ ዩሪየን ቲምበር ሁለት ግቦችን ከመረብ አሳርፏል። ቡካዮ ሳካ ሌላኛው ግብ ማስቆጠር የቻለ ተጫዋች ነው።

በጨዋታው አርሰናል ሁለት ወሳኝ ተጫዋቾቹ ማርቲን ኦዴጋርድ እና ቡካዮ ሳካን በጉዳት አጥቷል።

ሚካኤል አርቴታ ብዙ እየተወራለት የሚገኘው የ15 ዓመቱ ማክስ ዶውማንን ቀይሮ በማስገባት አጫውቷል። ፍፁም ቅጣት ምትም አስገኝቷል።

ሁለት የመጀመሪያ ጨዋታውን ያሸነፈው አርሰናል ከቶተንሃም እኩል ስድስት ነጥብ በማያዝ ሊጉን እየመራ ይገኛል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review