አምስት ግቦች የተቆጠሩበት ጨዋታ በሊቨርፑል አሸናፊነት ተጠናቀቀ

You are currently viewing አምስት ግቦች የተቆጠሩበት ጨዋታ በሊቨርፑል አሸናፊነት ተጠናቀቀ

AMN – ነሃሴ 19/2017 ዓ.ም

በሴንት ጀምስ ፓርክ የተካሄደው የኒውካስትል ዩናይትድ እና ሊቨርፑል ውጥረት የበዛበት ጨዋታ በሊቨርፑል 3ለ2 አሸናፊነት ተጠናቋል። የአሌክሳንደር ኢዛክ ኒውካስትልን ልቀቁኝ ማለቱ እና በሊቨርፑል መፈለጉ ሌላ ትርጉም ሰጥቶት የጀመረው ጨዋታ በስሜት የተሞላ ነበር። ሊቨርፑል ራያን ግራቨንበርች እና ሁጎ ኢኪቲኬ ባስቆጠሯቸው ግቦች 2ለ0 ቢመሩም ኒውካስትል ዩናይትድ እስከ መጨረሻው ደቂቃ ተፋልመው በቡርኖ ጉማይሬሽ እና ዊሊያም ኦሱላ ግቦች አቻ ሆነው ነበር።

ተቀይሮ የገባው የ16 ዓመቱ ባለተሰጥኦ ሪዮ ንጉሞሃ ሊቨርፑልን አሸናፊ አድርጓል። ብዙ እየተነገረለት የሚገኘው እና የፊታችን አርብ 17 ዓመት የሚሞላው ንጉሞሃ በሊቨርፑል ታሪክ በእድሜ ትንሹ ግብ አስቆጣሪ ሆኗል። ቀዮቹ በመጨረሻ 18 የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ በኒውካስትል ዩናይትድ አልተሸነፉም።

ኒውካስትል ዩናይትድ አንቶኒ ጎርደንን በቀይ ካርድ ጆሊንተን እና ሳንድሮ ቶናሊን በጉዳት ቢያጣም ከጨዋታው ነጥብ ለማግኘት ያደረገው ፍልሚያ አስደናቂ ነበር። ምንም እንኳን ጨዋታውን ቢያሸንፍም ክፍተቶች የነበሩበት ሊቨርፑል የፊታችን እሁድ ከአርሰናል ጋር በአንፊልድ ይጫወታል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review