ከ300 በላይ ወጣቶች በተሳተፉበት የቻይና የክህሎት ውድድር ኢትዮጵያዊያን የወርቅ፣ የብርና የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ ላደረጉ ወጣቶች አቀባበል ተደረገ

You are currently viewing ከ300 በላይ ወጣቶች በተሳተፉበት የቻይና የክህሎት ውድድር ኢትዮጵያዊያን የወርቅ፣ የብርና የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ ላደረጉ ወጣቶች አቀባበል ተደረገ

AMN ነሐሴ 20/2017

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በቻይና በተካሄደው የክህሎት ውድድር አሸናፊ ለሆኑት ወጣቶች ትናንት በቢሯቸው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከብሪክስ አባል ሀገራት የተውጣጡ ከ300 በላይ ወጣቶች በተሳተፉበት የቻይና የክህሎት ውድድር ኢትዮጵያዊያን የወርቅ፣ የብርና የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆነዋል።

የውድድሩ አሸናፊዎች እንደ ሀገር የተጀመረው ”ክህሎት ኢትዮጵያ” ፕሮግራም በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድንሆን አስችሎናል ብለዋል።

በውድድሩ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ የሆነው ወጣት ዘላለም እንዳለው በመድረኩ ባቀረበው የዲጂታል ግብርና አካል የሆነ ስማርት የመስኖ መቆጣጠሪያና መከታተያ የፈጠራ ሥራ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸልሟል።

ያቀረበው የፈጠራ ሃሳብ በግብርና ዘርፍ የሚያጋጥመውን ተግዳሮት በዲጂታል መንገድ በመታገዝ ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል መሆኑን ተናግሯል።

ሁለተኛ የወጣው ወጣት አቤኔዘር ተከስተ በበኩሉ በፈጠራ ባዳበረው በማንዋል የሚሰራ የፕላስቲክ ቅርጽ ማውጫ የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ መሆኑን ተናግሯል።

የሰራው ማሽን በአነስተኛ ዋጋ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የፕላስቲክ ቁሳቁሶችን ማምረት እንደሚችል አስታውቋል፡፡

የአንድን ሀገር ብልፅግና ለማረጋገጥ የክህሎት ልማት ወሳኝ መሆኑን የተናገረው አቤኔዘር የጀመረውን የክህሎት ልማት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

ወጣት ነቢሀ ነስሩ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ የተመሰረተና በሆስፒታሎች ታማሚዎች ነርስ ለመጥራት የሚያስችላቸውን የጥሪ “Nurse calling System” የፈጠራ ሀሳብ ለውድድር አቅርባ ሶስተኛ በመውጣት የነሐስ ሜዳሊያ መሸለሟን መናገሯን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የፈጠራ ሃሳቡ በታካሚዎች እና በነርሶች መካከል ያለውን የተግባቦት ሂደት ዲጂታላይዝ በማድረግ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን ገልፃለች።

በክህሎት ኢትዮጵያ ያገኘችው ስልጠና በውድድሩ ውጤታማ እንድትሆን እንዳስቻላትም ጠቅሳለች።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review