በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሦስተኛ ሳምንት በሜዳው አንፊልድ አርሰናልን ያስተናገደው ሊቨርፑል 1ለ0 አሸነፏል።
በተጠበቀው ልክ ጥራት ያለው ፉክክር ያልታየበት ጨዋታ እስከ 83ኛው ደቂቃ ግብ አልተቆጠረበትም። ሁለቱም ቡድኖች የጠራ የግብ ዕድል መፍጠር ተስኗቸው ታይተዋል።
ይበልጥ በታክቲክ የታጠረው ጨዋታ በዶሚኒክ ሶቦስላይ ድንቅ የቅጣት ምት ግብ ተጠናቋል። አርሰናል የውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ሽንፈት ሲገጥመው ሊቨርፑል በአሸናፊነቱ ቀጥሎ በዘጠኝ ነጥብ የሊጉ መሪ ሆኗል።
በጨዋታው በአርሰናል በኩል ወሳኝ ተከላካዩ ዊሊያም ሳሊባ ሲጎዳ ኤቤሬቺ ኤዜ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል። አሸናፊው ሊቨርፑል ኢብራሂማ ኮናቴ እና ፍሎሪያን ቨርትዝ ጨዋታው ሊጠናቀቅ አካባቢ በጉዳት ተቀይረው ወጥተዋል።
አርሰናል በፕሪምየር ሊጉ ከስድስት ጨዋታ በኋላ በሊቨርፑል ተሸንፏል።
በሸዋንግዛው ግርማ