የአፍጋኒስታን ምስራቃዊ ክፍል በሬክተር ስኬል 6 በሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመታ

You are currently viewing የአፍጋኒስታን ምስራቃዊ ክፍል በሬክተር ስኬል 6 በሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመታ

AMN ነሃሴ 26/2017

ምስራቅ አፍጋኒስታን በሬክተር ስኬል 6 በሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ የተመታ ሲሆን ርዕደ መሬቱ 8 ኪሎ ሜትር ጥልቀት እንዳለዉ ተነግሯል።

በተከሰተዉ የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ 20 ሰዎች መሞታቸዉን እና ከ100 የሚበልጡት ደግሞ ቆስለዉ በሆስፒታል እየታከሙ በመሆናቸዉን የአካባቢዉ ባለስልጣናት ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በምስራቅ አፍጋኒስታን በፖኪስታን ድንበር ተራራማ አካባቢዎች የተከሰተዉን የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ተከትሎ በርካቶች በፍርስራሽ ስር መሆናቸዉን ከታሊባን መንግስት የተገኙ ምንጮች አመላክተዋል።

እንደ ዘገባዉ ከሆነ የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ ይችላል ተብሎ ተሰግቷል።

ሰብአዊ ድርጅቶችም የነፍስ አድን ጥረቱን እንዲያግዙ የአካባቢዉ ባለስልጣናት አሳስበዋል።

ከመሬት መንሸራተቱ እና ከጎርፍ አደጋዉ ጋር በተያያዘ ሰብአዊ ድጋፎችን ማድረስ የሚቻለዉ በሂሊኮፕተር ብቻ መሆኑን ቢቢሲ ጨምሮ ዘግቧል።

የመሬት መንቀጥቀጡ ከካቡል እስከ ፓኪስታን ዋና ከተማ ኢስላማባድ በ300 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ያሉ ሕንፃዎችን ማናወጡም ተነግሯል።

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review