ከአገር ዉጭ ወጥተዉ መታከም ለማይችሉ ታማሚዎች እና ቤተሰብ ትልቅ እፎይታ የሚሰጥ የስትሮክ ሕክምና ማዕከል ሊገነባ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ

You are currently viewing ከአገር ዉጭ ወጥተዉ መታከም ለማይችሉ ታማሚዎች እና ቤተሰብ ትልቅ እፎይታ የሚሰጥ የስትሮክ ሕክምና ማዕከል ሊገነባ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ

AMN – ነሐሴ 27/2017 ዓ.ም

ከአገር ዉጭ ወጥተዉ መታከም ለማይችሉ ታማሚዎች እና ቤተሰብ ትልቅ እፎይታ የሚሰጥ የስትሮክ ሕክምና ማዕከል ሊገነባ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፤ ስትሮክ እና ሌሎችም ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደሆነ መረጃዎች ማመላከታቸውን ገልፀዋል ።

ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ የኢትዮዽያ ስትሮክ ፋዉንዴሽን በመዲናዋ የተሟላ የስትሮክ ሕክምና ማዕከል (comprehensive stroke service Center ) ለመገንባት ላሳዩት ተነሳሽነትም አመስግነዋል፡፡

ማዕከሉ ተገንብቶ ስራ ሲጀምር ከአገር ዉጭ ወጥተዉ መታከም ለማይችሉ ታማሚዎች እና ቤተሰብ ትልቅ እፎይታ የሚሰጥ ሲሆን በአፍሪካ አህጉር ደረጃ እንኳ በጣም ውስን በሆኑ አገራት ብቻ የሚሰጥ በመሆኑ እንደ አገር ለጀመርነዉ የጤና ቱሪዝምም በዉጭ ምንዛሬ ግኝት የሚኖረዉ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ጉልህ ነዉ ብለዋል።

ከንቲባዋ፤ የከተማ አስተዳደሩ ለስትሮክ ሕክምና ማዕከል መገንባት መሬት ከማቅረብ ጀምሮ ሌሎች ድጋፎችን እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡

መላዉ የከተማችን ነዋሪዎች ስትሮክን ጨምሮ ሌሎችም ተላላፊ ያልሆኑ ደዌዎችን አስቀድሞ መከላከያዉ መንገድ የአኗኗር ዘይቤ በመሆኑ ለዚህም ታልመዉ በተሰሩ የከተማችን የእግረኛ መንገዶች ፣ የስፖርት ማዕከላት እንዲጠቀሙ ከንቲባዋ መክረዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review