የአዲስ አበባ ከተማ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጳጉሜን 1 የፅናት ቀንን በተለያዩ መርሃ ግብሮች እያከበረ ይገኛል።
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ የጥቁር ህዝቦች ድል ተምሳሌት የሆነችው በህዝቦቿ አንድነት መሆኑን ተናግረዋል።
አሁንም በኢትዮጵያ ድህነትን ለማስወገድ እና ሰላምን ለማፅናት ሌት ተቀን የሚሰራ ህዝብ አለ ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው፣ ይህን የፅናት ተምሳሌት የሆነ ተግባርንም በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ መድገም ይገባል ብለዋል።
በመድረኩም የፓናል ውይይትን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ መርሃ ግብርሮች እየተከናወኑ ይገኛሉ።
በራሄል አበበ