የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቶክዮ ለሚካፈለው የአትሌቲክስ ልዑክ በስካይ ላይት ሆቴል ሽኝት እያደረገ ይገኛል።
በመርሃግብሩ ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካን ጨምሮ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ አባላት ፣ አትሌቶች እንዲሁም አሰልጣኞች ተገኝተዋል።
ከመስከረም 3 እስከ 11 ለሚካሄደው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና 36 አትሌቶች እና 12 አሰጣኞችን ጨምሮ አጠቃላይ 65 የልዑክ ቡድን አባላት ወደ ስፍራው ያቀናሉ።
በዮናስ ሞላ