ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎችን የፊት ገፅ ተቆጣጥሯል

You are currently viewing ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎችን የፊት ገፅ ተቆጣጥሯል

AMN – ጳጉሜን 4/2017 ዓ.ም

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከ14 ዓመታት የግንባታ ሂደት በኋላ በዛሬው ዕለት በደማቅ ስነ-ስርአት እየተመረቀ ይገኛል፡፡

ይህንን ዳግማዊ አድዋ፤ ኢትዮጵያውያን በተባበረ የይቻላል መንፈስ ለፍፃሜ የበቃ ግድብ የምረ ስነ ስርዓት ከግድቡ ቦታ ጀምሮ በመላው የሃገሪቱ ክፍል በድምቀት ይገኛል፡፡

ይህ የምረቃ ስነ-ስርአት ታዲያ ከሃገር ውስጥ ሚዲያዎች አልፎ ታታላቅ ዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎች የፊት ገፆቻቸው ላይ ይዘውት ወጥተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቁን ግድብ አስመርቃለች ሲል በማህበራዊ ትስስር ገፁ በፊት ገፅ ይዞ የወጣው ሮይተርስ ነው፡፡

ብሉምበርግ፣ ዘ ኢንዲፔንደንት፣ ሮይተርስ፣ ቢቢሲ፣ ፍራንስ 24፣ አሶሼትድ ፕሬስ፣ አናዶሉ እና የሌሎችም አለም አቀፍ ሚዲያዎችም ሚዲያዎች እየዘገቡት ይገኛሉ፡፡

የኬኒያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በግድቡ ምረቃ ላይ የተገኙ ሲሆን በጉባ ሰማይ ስር እየተከናወነ ያለውን ይህንን ታላቅ እና ድንቅ ሁነት በፌስ ቡክ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ለተከታዮቻቸው አጋርተዋል፡፡

በያለው ጌታነህ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review