ዓባይ የቤታችን ብርሃን ሆኖ በተስፋ ነጋችንን ያበራል ሲል የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ገለፀ፡፡
አዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የግድቡን መመረቅ አስመልክቶ ባስተላለፈው የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ፤ የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የአብሮነታችን፣ የሉዓላዊነታችን፣ የአድነታችን አሻራ ያረፈበት እና በፍቅር የተፃፈ የመሰዋዕትነት ታሪካችን ጭምር መሆኑን ገልጿል፡፡
ዓባይ የጉባ ከፍታ ላይ የተገደበ ወንዝ ብቻ አይደለም፤ የሃይማኖት አባቶች ጸሎት እና የእናቶች እንባ፤ የመሪዎችና የህዝባችን ቁርጠኝነት ጭምር ነው ሲል ጉባኤው አክሏል፡፡
ጉባኤው ለኤ ኤም ኤን በላከው የደስታ መልዕክት እንደገለጸው የታላቁ የሕዳሴው ግድብ ብሔራዊ ጥቅምን ለሚረዳ ሰው ትርጉሙ ጥልቅ እና ብዙ ነው ብሏል።
ዓባይ የቤታችን ብርሃን ሆኖ በተስፋ ነጋችንን ጭምር ያበራል ያለው መግለጫው ፤ ለመላው ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንኳን ለዚህ ታላቅና ታሪካዊ ቀን አደረሳችሁ ሲል መልካም ምኞቱን ገልጿል።