ጳጉሜን 5 የነገው ቀን ”ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ” በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ መርሃ ግብሮች እየተከበረ ነው

You are currently viewing ጳጉሜን 5 የነገው ቀን ”ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ” በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ መርሃ ግብሮች እየተከበረ ነው

AMN ጳጉሜን 5/2017

በዲጂታል ቴክኖሎጂ የጎለበተች ፣ የምግብ ሉዓላዊነቷን ያረጋገጠች ለችግሮች የማትበገር ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ሁላችንም የበኩላችንን መወጣት አለብን ሲሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ/ር) ገለፁ።

ጳጉሜን 5 የነገው ቀን ”ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ” በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ መርኃ ግብሮች እየተከበረ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤የነገዋ ኢትዮጵያን ለመፍጠር ዛሬ ላይ ተቋማትና አመራር አባላት በጥበብና በራዕይ ስለሚመሩበት ውይይት ይካሄዳል።

ይህም የዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ አርቲፊሻል ኢንተሌጀንስ እና ኢኖቬሽን የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ፣ አይበገሬነትን ለማጽናት እና የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ አጠቃቀምን ለመረዳት ያስችላል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ታሪክ ከእንግዲህ ሲነገር ህልውናን የማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን የመቻል እና ለሌላውም የመትረፍ ጭምር እንደሆነ መገንዘብ እና ሌሎችንም ማስገንዘብ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ትናንት የተመረቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአንድ ዘመን ታላቅ ለውጥ ማሳያ እንደሆነ ተናግረው፤ የመጨረሻ ሳይሆን የአዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለቤት፣ ለኢንዱስትሪ የኤሌትሪክ ኃይል እንደሚያቀርብ ሁሉ፤ ቴክኖሎጂን እና ኢኖቬሽንን የሚያለመልም መሆኑን አመልክተዋል።

በተለይም ለኢኮኖሚያዊ ሽግግር ሞተር በመሆን ዜጎች ከአዳዲስ እድሎች ጋር የሚያስተሳስር እና የመጪ ጊዜ መንገድን ብሩህ የሚያደርግ መሆኑን ነው የተናገሩት።

በዲጂታል የጎለበተች፣ የምግብ ሉዓላዊነቷን ያረጋገጠች እና ለችግሮች የማትበገር ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ሁላችንም የበኩላችንን መወጣት አለብን ማለታዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ነገዋን የምትጠብቅ ሳይሆን ነገዋን በራሷ የምትፈጥር ኢትዮጵያን እንገንባ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review