የህዳሴን ግድብ ማጠናቀቃችን ለሌላ ስኬት እና ድል የሚያነሳሳን ነው ሲሉ አቶ በላይ ደጀን ገለፁ

You are currently viewing የህዳሴን ግድብ ማጠናቀቃችን ለሌላ ስኬት እና ድል የሚያነሳሳን ነው ሲሉ አቶ በላይ ደጀን ገለፁ

AMN – መስከረም 02/2018 ዓ.ም

የህዳሴን ግድብ ማጠናቀቃችን ለሌላ ስኬት እና ድል የሚያነሳሳን ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ በላይ ደጀን ገለፁ፡፡

በህብረት ችለናል በሚል መሪ ቃል ከ300ሺ በላይ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የተሳተፉበት የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ዛሬ ማለዳ ተካሂዷል፡፡

በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ በላይ ደጀን፤ የሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና ማማ ለመድረስ የሚያስችላት ቁልፍ መሳሪያ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

የህዳሴን ግድብ ማጠናቀቃችን ለሌላ ስኬት እና ድል የሚያነሳሳን ነው ያሉት አቶ በላይ፤ ግድቡ አገር የሚጠቅም እንዲሆን መንግስትና ሕብረተሰቡ ያደረጉት የአርበኝነት ተጋድሎ ታሪክ ሲዘክረው የሚኖር ታላቅ ገድል ነው በማለት ተናግረዋል፡፡

ለሕዳሴ ግድብ የወጣቶችና የስፖርት ቤተሰቦች ተሳትፎ ከፍተኛ እንደነበር ያስታወሱት አቶ በላይ፤ በቀጣይ በሀገራቸው ሁለንተናዊ ልማት እና ሰላም ላይ ግንባር ቀደም ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review