ቡርኪና ፋሶ ለሁሉም የአፍሪካ ተጓዦች ከቪዛ ነፃ ጉዞን ፈቀደች

You are currently viewing ቡርኪና ፋሶ ለሁሉም የአፍሪካ ተጓዦች ከቪዛ ነፃ ጉዞን ፈቀደች

AMN – መስከረም 2/2018 ዓ.ም

ቡርኪና ፋሶ ለሁሉም የአፍሪካ ተጓዦች ከቪዛ ነፃ ወደ ሃገሪቷ መግባት የሚያስችል ፖሊሲን አስተዋውቃለች፡፡

ሰዎች እና ሸቀጦች ወደ ሀገሪቱ የሚገቡበትን ሁኔታ ይበልጥ ምቹ ለማድረግ እና ቃጣናዊ ትስስርን ለማጠናከር በማለም የተወሰነው ይህ ውሳኔ፤ ተጓዦች ጉዟቸውን ለማፀደቅ በበይነ መረብ በማመልከት ያለ ምንም የቪዛ ክፍያ ወደ ሃገሪቱ ለመግባት የሚያስችላቸው ይሆናል፡፡

በዚህም ሃገሪቱ ለአፍሪካ ሃገራት የጉዞ መስፈርቶችን ካቀለሉ ከነ ጋና፣ ሩዋንዳ እና ኬንያ ጋር እንድትሰለፍ አስችሏታል፡፡

ውሳኔው ከፈረንጆቹ 2022 ጀምሮ ስልጣን ላይ ያሉትን የሃገሪቱ ወታደራዊ መሪ ኢብራሂም ትራኦሬን የፓን አፍሪካኒዝም ሃሳብ የሚያንፀባርቅ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ይህ ውሳኔ የሃገሪቱን የቱሪዝም ዘርፍ ለማሳደግ እና ባህሏንም በማስተዋወቅ ዓለም አቀፍ ትኩረትንም እንድትስብ ያደርጋል ተብሎ ታምኗል፡፡

ሆኖም የሃገሪቱ ውሳኔ ከጎረቤት ሃገሮቿ ጋር ያላትን ግንኙነት ስለማጠናከሩ እርግጠኛ መሆን እንደማይቻልም ዘገባው አመላክቷል፡፡

ቡርኪና ፋሶ፣ ማሊ እና ኒጀር ሌላ ህብረት ለመፍጠር የምዕራብ አፍሪካ መንግስታት የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) ለቀው መውጣታቸውን ዘገባው አስታውሷል፡፡

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review