ድርቤ ወልተጂ በቶክዮ የዓለም አትሌቲክስ ውድድር አትሳተፍም

You are currently viewing ድርቤ ወልተጂ በቶክዮ የዓለም አትሌቲክስ ውድድር አትሳተፍም

AMN – መስከረም 2/2018 ዓ.ም

ከአበረታች ንጥረ ነገር ምርመራ ጋር በተያያዘ ውዝግብ ውስጥ የገባችው ድርቤ ወልተጂ የዓለም አትሌቲክስ ውድድር ላይ እንደማትሳተፍ የዓለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድቤት አረጋግጧል፡፡

አትሌቷ ለኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የዶፒንግ ምርመራ ናሙና ለመስጠት ፍቃደኛ መሆን አልቻለችም።

በዚህ ምክንያት የአትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት(AIU)፤ አትሌቷ በጊዜያዊነት ከውድድር እንድትታገድ ለዓለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት (CAS) ያቀረበው ይግባኝ ተቀባይነት በማግኘቱ ድርቤ በውድድሩ አትሳተፍም።

ትልቅ ተስፋ የተጣለባት የ23 ዓመቷ አትሌት ሀገሯን በ1500 ሜትር እንድትወክል ተመርጣ ወደ ቶክዮ አቅንታ ነበር።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review