የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል

You are currently viewing የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል

AMN – መስከረም 3/2018 ዓ.ም

በ2017 የትምህርት ዘመን የተሰጠው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት በነገው ዕለት ይፋ ይሆናል።

የትምህርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፤ የፈተና ውጤቱን አስመልክቶ በነገው ዕለት ከ10 ሰዓት ጀምሮ ለመገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ ይሰጣል።

የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ መሰጠቱ ይታወሳል።

በተፈጥሮ ሳይንስና በማህበራዊ ሳይንስ በአጠቃላይ 608 ሺህ 742 ተማሪዎች ተመዝግበው 581 ሺህ 905 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸወን ኢዜአ ዘግቧል።

ከተፈታኞቹ መካከልም 134 ሺህ 828 ተማሪዎች በበይነ መረብ የተፈተኑ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ ተማሪዎች ደግሞ በወረቀት ተፈትነዋል።

ፈተናው በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በተቋቋሙ 216 የመፈተኛ ማዕከላት በበይነ መረብ በአራት ዙር እንዲሁም በወረቀት በሁለት ዙር ተሰጥቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review