የብላክ ላየን ሰርከስ ቡድን የሆነው ትሩፕ አዲስ አበባ በሩሲያ በተካሄደው የሰርከስ ኒውክሊን የብር መዳሊያ አሸናፊ ሆነ

You are currently viewing የብላክ ላየን ሰርከስ ቡድን የሆነው ትሩፕ አዲስ አበባ በሩሲያ በተካሄደው የሰርከስ ኒውክሊን የብር መዳሊያ አሸናፊ ሆነ

AMN መስከረም 6/2018

የብላክ ላየን ሰርከስ ቡድን የሆነው ትሩፕ አዲስ አበባ በሩሲያ አገር በተካሄደው የሰርከስ ኒውክሊን / Nikulin Circus Moscow/ እጅግ ድንቅ በሆነ አቀራረብና ፉክክር የብር መዳሊያ አሸናፊ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ቡድኑ ባለፈው አመት በፈረንሳይ በተካሄዱት የአለማችንን አንጋፋው ሰርከስ ፌስቲቫል ሰርከስ ሞንቴካርሎ/Cirque Monte Carlo/ ላይ የነሃስ አንዲም በቦርዴክ አለም አቀፍ ፌስቲቫል/11th Cirque de Bayeux,France/ ላይ የወርቅ ዋንጫ አሸናፊ መሆን የቻለ ድንቅ የሰርከስ ቡድን መሆኑ ተገልጿል፡፡

አባላቱ ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰርከስ ፕሬዝዳንት አርቲስት ተክሉ አሻግርና የአዲስ አበባ ሰርከስ ማህበር ም/ፕሬዝዳንት አርቲስት ቢኒያም እንዳለ አቀባበል አድርገዉላቸዋል፡፡

በአንተነህ አለማየሁ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review