የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ስኬት ሌሎች ታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶችን የመስራት አቅም እንዳለን የታየበት ነው ሲሉ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) ተናገሩ

You are currently viewing የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ስኬት ሌሎች ታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶችን የመስራት አቅም እንዳለን የታየበት ነው ሲሉ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) ተናገሩ

AMN – መስከረም 7/2018 ዓ.ም

የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ስኬት ሌሎች ታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶችን የመስራት አቅም እንዳለን የታየበት ነው ሲሉ የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቁን ተከትሎ “በህብረት ችለናል!” በሚል ሃሳብ በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ አስተዳደር በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ የተገኙት የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር)፤ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ስኬት ሌሎች ታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶችን የመስራት አቅም እንዳለን የታየበት መሆኑን ገልጸዋል።

የግድቡ ግንባታ ስኬት ሌሎች ታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶችን በራስ አቅም የመስራትና የማጠናቀቅ የተደመረ አቅም የታየበት መሆኑንም አንስተዋል።

በጋራ ጥረታችን ለስኬት የበቃው የሕዳሴ ግድብ የሁላችንም የደስታ ምንጭ ሆኗል ብለዋል።

የግንባታው እቅድ እውን እንዳይሆን ከውጭ ጫናዎች፤ ከውስጥ የበዙ መሰናክሎች ቢገጥሙም በጽናትና በህብረ ብሄራዊ አንድነት ማሳካት ችለናል ሲሉም ተናግረዋል።

በሸገር ከተማ አስተዳደር ለገጣፎ ለገዳዲ በተካሄደው ሰልፍ የተሳተፉት ነዋሪዎች በበኩላቸው፤ የግድቡ መጠናቀቅ ለሀገራችን ትልቅ ተስፋ የሰነቀ ነው ብለዋል።

በቀጣይም ሰላማችንን በማጽናት የተጀመሩ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ የድርሻችንን ለመወጣት ተዘጋጅተናል ብለዋል።

በመሀመድኑር ዓሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review