ሀገር ተረካቢ ታዳጊዎች ለሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ዝንባሌ ኖሯቸው እንዲያድጉ የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ

You are currently viewing ሀገር ተረካቢ ታዳጊዎች ለሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ዝንባሌ ኖሯቸው እንዲያድጉ የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ

AMN መስከረም 10/2018

ሀገር ተረካቢ ታዳጊዎች ለሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ዝንባሌ ኖሯቸው እንዲያድጉ የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ይህ ትውልድ እኛ ያለፈን ዕድል ሊያልፈው አይገባም፤ ሊወርስ የሚገባውም ግጭት ጦርነት እና ችግር መሆን የለበትም ሲሉም ገልጸዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በክረምት ስልጠና ሲወስዱ የቆዩ ተማሪዎች ምርቃት ላይ ተገኝተናል ብለዋል፡፡

መንግስት ባለፉት 3 ዓመታት በክረምት መርሃ ግብር ሀገር ተረካቢ ታዳጊዎች ለሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ዝንባሌ ኖሯቸው እንዲያድጉ የሚያስችል ስልጠናን እየሰጠ ይገኛል ነው ያሉት።

ይህም ዘመኑን የሚዋጅና ከሰው ሰራሽ አስተውሎት አብዮት ጋር የሚናበብ ሀገራዊ ልማትና ትውልድ ግንባታን ለመፍጠር ያስችላል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ለታዳጊዎች እየተሰጠ ያለው ስልጠናም ቴክኖሎጂን በመጠቀም ችግር ፈቺ የፈጠራ ሀሳቦችን እንዲያፈልቁና በዘርፉ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ዓላማ ያደረገ ነው ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

በሁሉም ዘርፍ የተማረ እና የነቃ ትውልድ የማፍራት ስራችን ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፣ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አመራሮች ይህ ውጥን ዕውን እንዲሆን ለሚያደርጉት ጥረት ምስጋናዬን ማቅረብ እወዳለሁ ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review