በኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት የተዘጋጀው “ብርሃን ፈንጣቂው ዓባይ” በሚል ርዕስ የተጻፈው መፅሀፍ በዛሬው እለት ተመርቋል፡፡
በምረቃ ፕሮግሩሙ ላይ የተገኙት የፕረስ ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መሳፍንት ተፈራ፣ መፅሀፉ የኢትዮጵያዊያን የዘመናት ቁጭት የሆነውን የዓባይ ገድል የሚዘክር ነው ብለዋል።
ግድቡ በተለይ ላለፉት 14 ዓመታት ያሳለፈውን ውጣ ውረድ ሰንዶ ለትውልድ በማሻገር ትልቅ ድርሻ አለው ያሉት ደግሞ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተሰፋሁን ጎበዛይ ናቸው::
ብርሃን ፈንጣቂው አባይ የሚለው መፅሃፍ በሶስት ምዕራፎች የተከፋፈለ እና 252 ገፆች ያሉት ነው::
በምረቃ መርሃግብሩ ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ደራሲዎችና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ተገኝተዋል::
በጺዮን ማሞ