የኢሬቻ በዓል ባህላዊ ትውፊቱን ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ የታሪክና የባህል አጥኚ ምሁራን ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ

You are currently viewing የኢሬቻ በዓል ባህላዊ ትውፊቱን ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ የታሪክና የባህል አጥኚ ምሁራን ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ

AMN – መስከረም 22/2018 ዓ.ም

የኢሬቻ በዓል ባህላዊ ትውፊቱን ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ የታሪክና የባህል አጥኚ ምሁራን ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የፓናል ውይይት አካሂዷል።

በውይይት መድረኩ ላይ የከተማዋ የተለያዩ የስራ ኃላፊዎች፣ አባ ገዳዎች፣ወጣቶች እንዲሁም መምህራን ተሳታፊ ሆነዋል።

ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ለዓመቱ በረከት ፈጣሪውን የሚያመሰግንበት እንዲሁም መጪው ዘመን የሰላም እንዲሆን የሚለምንበት በዓል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ኢሬቻ የገዳ ስርሃት አንዱ መገለጫና በውስጡ በርካታ ትውፊቶችን የያዘ የአደባባይ በዓል ነው ያሉት ኃላፊው፤ ይህንን ለትውልድ ለማሻገር ምሁራን ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል።

የቱሪዝም ዘርፉን ከማነቃቃት አንፃር ኢሬቻ ያለው አበርክቶ ከፍተኛ መሆኑንም ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

በራሄል አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review