በ7ኛዉ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ ብሬንትፎርድ ከማንችስተር ሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ ትኩረት አግኝቷል

You are currently viewing በ7ኛዉ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ ብሬንትፎርድ ከማንችስተር ሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ ትኩረት አግኝቷል

AMN-መስከረም 25/2018 ዓ.ም

በ7ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ ዛሬ አምስት ጨዋታዎች ይከናወናሉ።

ብሬንትፎር በሜዳው ጌትች ኮሚኒቲ ስታዲየም ምሽት 12:30 ማንችስተር ሲቲን የሚያስተናግድበት ጨዋታ የበለጠ ትኩረት አግኝቷል።

በኪት አንድሪውስ የሚመራው ብሬንትፎርድ በሜዳው የሚቀመስ ቡድን አይደለም። አስቶንቪላ ፣ ቼልሲ እና ማንችስተር ዩናይትድን ገጥሞ ሰባት ነጥብ ወስዷል። ባሳለፍነው ሳምንት ዩናይትድን 3ለ1 ረተው የበለጠ የተነቃቁት ብሬንትፎርዶች ለማንችስተር ሲቲ ፈተና ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በመከላከሉ ረገድ አስተማማኝነት የጎደለው ሲቲ የብሬንትፎርድን ረጃጅም እና የቆሙ ኳሶች አደጋ ፈጣሪ ይሆኑበታል። ማንችስተር ሲቲ አጥቂው አርሊንግ ሃላንድ በጥሩ ብቃት ጀምሮለታል። ኖርዌያዊው የ24 ዓመት አጥቂ በሁሉም ውድድሮች 11 ግቦችን በስሙ አስመዝግቧል።

በዛሬውም ጨዋታ ልዩነት ፈጣሪ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። በሲቲ በኩል ራያን ሸርኪ ከጉዳቱ አገግሞ ወደ ስብስቡ ተመልሷል።

በሌሎች የዛሬ የሊጉ ጨዋታዎች አስቶንቪላ ከ በርንሌይ ፣ ኤቨርተን ከ ክሪስታል ፓላስ ፣ ኒውካስትል ዩናይትድ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት እንዲሁም ወልቭስ ከ ብራይተን በተመሳሳይ 10 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ይጀምራሉ።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review