የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት አካሄድ ከታዛቢነት ወደ አጀንዳ ተላሚነት መሸጋገሩን የኢፌድሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ተናገሩ

You are currently viewing የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት አካሄድ ከታዛቢነት ወደ አጀንዳ ተላሚነት መሸጋገሩን የኢፌድሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ተናገሩ

AMN- መስከረም 26/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ የጂኦ ስትራቴጂያዊ ቁመና በመደርጀት ላይ እንደሚገኘ እና ከታዛቢነት ወደ አጀንዳ ተላሚነት እንዲሁም ተጽእኖ ፈጣሪነት ተቀይሯል ሲሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ተናገሩ።

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና የፌዴሬሽን ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ ሥርዓት የሁለቱ ምክር ቤቶች አፈጉባዔዎችና የምክር ቤቶቹን አባላት ጫምሮ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሄዷል፡፡

የሁለቱን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ በይፋ ያስጀመሩት ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ የውጭ ጉዳይ ግንኙነታችን ማዕከል እና ማጠንጠኛ ብሄራዊ ጥቅም እና የዜጎች ክብር ነው ሲሉ ተናረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በድንበር ተሻጋሪ ሀብቶቿ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ስትቀበል በዛው ልክ የባህር በር የማግኘት መብቷን ማረጋገጥ ይኖርባታል ሲሉም አክለዋል።

ኢትዮጵያ ከውሀ ጋር በተያያዙ ሁለት አበይት አጀንዳዎችን ለማሳካት ያልተቆራረጠ ሰላማዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች እየተደረጉ እንደሚገኙ ፕሬዝዳንቱ አንስተዋል።

እስካሁን በተደረጉ ጥረቶችም ሶስት ጉልህ ውጤቶች መገኘታቸውን የገለጹት ፕሬዝዳንቱ አንደኛው የህዳሴ ግድብ የነበረበትን ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጫና በመቋቋም ለውጤት እና ምርቃት ማብቃት እንደሆነ አብራርተዋል።

አስተማማኝ እና ዘላቂነት ያለው የባህር በር የማግኘት ፍትሀዊ ጥያቄ ጉዳይ ከፍ ወዳለ ደረጃ ከመሸጋጋሩ ባለፈ በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ የነበረው ቅቡልነት እያደገ መሆኑ ደግሞ ሁለተኛው ውጤት ሆኖ ተገልጿል።

ሶስተኛው በውጭ ሀገራት ለእንግልት ተጋልጠው የነበሩ ዜጎች በክብር ወደ ሀገራችው የመመለስ ስራ ሲሆን ይህ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው ጠቁመዋል።

በዳዊት በሪሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review