ኢትዮጵያ ከውሀ ጋር የተያያዙ ሁለት ዓበይት አጀንዳዎችን ለማሳካት ያልተቆራረጠ ሰላማዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን እያደረገች እንደምትገኝ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ተናገሩ፡፡
ኢትዮጵያ በድንበር ተሻጋሪ ሀብቶቿ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ስትቀበል በዛው ልክ የባህር በር የማግኘት መብቷን ማረጋገጥ ይኖርባታል ሲሉ አሳስበዋል።
አስተማማኝ እና ዘላቂነት ያለው የባህር በር የማግኘት ፍትሃዊ ጥያቄ ጉዳይ ከፍ ወዳለ ደረጃ ከመሸጋጋሩ ባለፈ፤ በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ የነበረው ቅቡልነት እያደገ እንደሚገኘም ተናግረዋል።
ባለፉት አመታት ከአለም ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ተጣጥሞ የሚቀጥል ራዕይ እና አላማ አንግበን በመንቀሳቀሳችን ሊደርስብን የሚችለውን ጫና ተቋቁመን ሀገራዊ ጥቅማችንን አስጠብቀናል ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ።
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና የፌዴሬሽን ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል።
በመክፈቻው ስነ-ስርአት ላይ ያለፈው አመት የመንግስት አፈጻፈም እና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ያቀረቡት ፕሬዝዳንት ታዬ፤ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት አካሄድ ከታዛቢነት ወደ አጀንዳ ተላሚነት መሸጋገሩን ገልጸዋል።
በዳዊት በሪሁን