የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና የንግድ ስምምነት ትግበራ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጉዳይ ላይ ያላትን የግንባር ቀደምትነት ሚናዋን በኢኮኖሚው ዘርፍ የሚደግም መሆኑን አቶ አደም ፋራህ ገለጹ

You are currently viewing የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና የንግድ ስምምነት ትግበራ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጉዳይ ላይ ያላትን የግንባር ቀደምትነት ሚናዋን በኢኮኖሚው ዘርፍ የሚደግም መሆኑን አቶ አደም ፋራህ ገለጹ

AMN መስከረም 29/2018 ዓ.ም

የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና የንግድ ስምምነት ትግበራ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጉዳይ ላይ ያላትን የግንባር ቀደምትነት ሚናዋን በኢኮኖሚው ዘርፍ የሚደግም መሆኑን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለጹ፡፡

ነጻ ቀጠናዉ የአፍሪካዊያን እጣ ፈንታ በአፍሪካዊያን መወሰን አለበት የሚለውን ግብ ያሳካችበት ነው ብለዋል።

አፍሪካዊያን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያለውን አዳጊ እና አጓጊ የኢኮኖሚ እድል እንዲጠቀሙ የሚረዳ የስምምነት ትግበራ መሆኑን ገልጸዋል ።

የንግዱ ዘርፍ አካላት ለሀገር እና ለዜጎች የሚተርፍ ስራዎች እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል ።

ለአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና የንግድ ስምምነት ትግበራ አስተዋጽኦ ላደረጉ ግለሰቦች ፣ የግሉ ዘርፍ እና የመንግስት ተቋማት እውቅና ተሰጥቷቸዋል ።

ነጻ የንግድ ቀጠናው በ1.4 ቢሊዮን የህዝብ ብዛትና ከ 3. 4 ትሪሊዮን ዶላር በላይ የዋጋ ድምር ያለው የሀገር ውስጥ ጥቅል ምርት ያላቸው የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራትን ያካተተ ነጻ የንግድ ቀጣና ነውም ብለዋል።

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review