አዲስ የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ መቀየር ለምን አስፈለገ?

You are currently viewing አዲስ የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ መቀየር ለምን አስፈለገ?

AMN መስከረም 30/2018

👉 በቀድሞው የትራንስፖርት አዋጅ ሲሰጡ የነበሩ የተሽከርካሪ መለያ ቁጥር ሰሌዳ አይነትና ምልክቶች፣ አመራረት፣ አሰረጫጨትና አወጋገድ ወቅቱ ከሚጠይቀዉ ተጨባጭ ሁኔታና የአገልግሎት አሰጣጡ ከዘርፉ ዕድገት ጋር ያልተጣጣመ መሆኑ፤

👉 ሀገሪቱ ተቀብላ ካጸደቀቻቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ያካተተ አለመሆኑ፣

👉 አሁን ከተደረሰበት እና ወደፊት አለም ከሚደርስበት የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎትና ዕድገት አንጻር አብሮ የሚሄድ ባለመሆኑ፣

👉 የአገልግሎት አሰጣጡ ምልልስ የበዛበት፣ ሀብትንና ጊዜን የሚያባክን በመሆኑ፣

👉 ተገልጋዩን ያላረካ፣ ለሙስናና መልካም አስተዳደር ችግሮች ያጋለጠ በመሆኑ፣

👉 የማምረትና የማሰራጨት ሰንሰለቱ ለቁጥጥር አመቺ አለመሆኑ፣

👉 ተመሳሳይ መለያ ቁጥሮች በሀገሪቱ በመበራከታቸዉ ፣

👉 ከተወገደ ተሽከርካሪ /በሞተ/ በኢንሹራንስ የተወገደ/ ተሽከርካሪን በጨረታ በመግዛት እንደ አዲስ በሞተ እንዲመዘገብ መደረጉ፣

👉 ትራንስፖርት ቢሮዎችን ለከፍተኛ ወጪ የዳረገ በመሆኑ፣

👉 የሀገር ውስን ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም የተሽከርካሪዎችን ሰሌዳ መለያ ቁጥር አይነትና ምልክቶችን ሀገራችን የተቀበለቻቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን መሰረት በማድረግ የመለያ ቁጥር አይነትና ምልክቶችን፣ የሠሌዳ አመራረትን፣ ስርጭትና አወጋገድ ላይ የሚታዩትን ክፍተት ለመዝጋት የተሽከርካሪዎች የመለያ ቁጥር እና ሰሌዳ ዓይነቶችና ምልክቶች መወሰኛና አገልግሎት መስጫ መመሪያ 1050/2017 አጸድቆ ወደ ስራ ገብቶአል፡፡ – ምንጭ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር

#አዲስሚዲያኔትዎርክ

#Ethiopia

#addisababa

#transportation

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review