በአውሮፓ ሀገራት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ምድብ ዘጠኝ ላይ የምትገኘው ኖርዌይ ስድስተኛ ተከታታይ ድሏን አሳክታለች።
በሜዳዋ እስራኤልን ያስተናገደችው ኖርዌይ 5ለ0 ማሸነፍ ችላለች።
በጨዋታ ፍፁም ቅጣት ምት ያመከነው ኧርሊንግ ሃላንድ ሀትሪክ ተሰርቷል። ተጨማሪ ሁለት ግቦችን የእስራኤል ተጫዋቾች በራሳቸው መረብ ላይ አሳርፈዋል።
46ኛ የብሔራዊ ቡድን ጨዋታውን ያደረገው ሃላንድ ያስቆጠራቸውን ግቦች 51 አድርሷል።
ለብሔራዊ ቡድኑ ሃትሪክ ሲሰራም ለስድስተኛ ጊዜ ሆኗል።
እ ኤ አ ከ1998 በኋላ ወደ ዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ለመመለስ የተቃረበችው ኖርዌይ በ18 ነጥብ ምድቧን እየመራች ትገኛለች።
በዚሁ ምድብ የምትገኘው ጣልያን ዛሬ ምሽት 3:45 ከኢስቶኒያ ጋር ትጫወታለች።
በሸዋንግዛው ግርማ