የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎችን ቀድሞ መከላከልና ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችል አቅም እየተገነባ እንደሚገኝ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ

You are currently viewing የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎችን ቀድሞ መከላከልና ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችል አቅም እየተገነባ እንደሚገኝ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ

AMN – ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም

የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎችን ቀድሞ መከላከልና በራስ አቅም ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችል የተቀናጀ አቅም እየተገነባ መሆኑን የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሸነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም(ዶ/ር) ገልጸዋል።

ዓለም አቀፍ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ቀን “ለአደጋ ስጋት አይበገሬነት ግንባታ ትኩረት እንስጥ” በሚል መሪ ሃሳብ በአፋር ክልል በሰመራ ከተማ ተከብሯል።

በሁነቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሸነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም(ዶ/ር) ፤ በተለይም ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ምጣኔ ሃብት መገንባት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

በተፈጥሮ የሚመጡ አደጋዎችን ቀድሞ የመከላከልና በራስ አቅም ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችል የተቀናጀ አቅም መፍጠር እንደሚገባ አንስተው ለዚህም ዘላቂና የተቀናጀ አሰራር መፍጠር ያስፈልጋል ነው ያሉት።

በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አክሊሉ ታደሰ፤ በተለይም የግብርና ልማት ስራዎችን በማስፋትና ምርታማነትን በማሳደግ ለአደጋዎች ጥንቃቄና ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችል አቅም መገንባት እንደሚገባ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የቤተሰብ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና ሀገራዊ የኢኮኖሚ አቅምን በማሳደግ የምግብ ሉአላዊነትን ማረጋገጥ የጋራ አጀንዳ ሆኖ በተጠናከረ መልኩ መቀጠል አንዳለበትም አስገንዝበዋል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የአፋር ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ ኀላፊ አሊ መሐመድ፤ በክልሉ የሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎችን ቀድሞ የመከላከልና ፈጣን ምላሽ የመስጠት አቅም ለመፍጠር እየተሰራ ነው ብለዋል።

በመርሃ ግብሩ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ኖጎ(ዶ/ር)፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የአደጋ ስጋት አመራሮች ተሳትፈዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review