በአውሮፓ ሀገራት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ዛሬ ምሽት በርካታ ጨዋታውች ይደረጋሉ፡፡
እንግሊዝ እና ፖርቹጋል ተጋጣሚዎቻቸውን ከረቱ ለ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ያለፉ የመጀመሪያዎቹ የአውሮፓ ሀገራት ይሆናሉ፡፡ ምድብ 11 ላይ የተደለደለችው እንግሊዝ ከሜዳዋ ውጪ ላቲቪያን ትገጥማለች፡፡
በጀርመናዊው አሰልጣኝ ቶማስ ቱኸል የምትመራው እንግሊዝ ያደረገቻቸውን አምስቱንም ጨዋታ ምንም ግብ ሳይቆጠርባት ማሸነፍ ችላለች፡፡ ዛሬ ምሽት 3፡45 በሚደረገው ጨዋታ ሦስት ነጥቡን ካሳካች የዓለም ዋንጫ ተሳትፎዋን ታረጋግጣለች፡፡

ምድብ ስድስት ላይ የምትገኘው ፖርቹጋል ሀንጋሪን ታስተናግዳለች፡፡ በጆዜ አልቫላዴ የሚደረገው ጨዋታ በባለሜዳዋ ፖርቹጋል አሸናፊነት ከተጠናቀቀ በቀጥታ ሀላፊ መሆኗን ታበስራላች፡፡ ጨዋታው ምሽት 3፡45 ይጀምራል፡፡
ሦስቱንም ጨዋታዎች አሸንፋ በዘጠኝ ነጥብ ምድቧን የምትመራው ስፔን ከቡልጋሪያ ጋር ትጫወታለች፡፡ በዚሁ ምድብ አምስት የምትገኘው ቱርኪዬ ከጆርጂያ ጋር ምሽት 1 ሰዓት ላይ ጨዋታዋን ታከናውናለች፡፡
በሸዋንግዛው ግርማ