ኢትዮ ቴሌኮም የአጠቃቀም ተግዳሮትን ይፈታሉ ያላቸውን አገልግሎቶች በዛሬው ዕለት ይፋ አደረገ

You are currently viewing ኢትዮ ቴሌኮም የአጠቃቀም ተግዳሮትን ይፈታሉ ያላቸውን አገልግሎቶች በዛሬው ዕለት ይፋ አደረገ
  • Post category:ቢዝነስ

AMN – ጥቅምት 06/2018 ዓ.ም

ኢትዮቴሌኮም አጠቃቀምን የሚጨምሩ በክላውድ ላይ የተመሰረቱ ዘኔክሰስ ስማርት ዲቫይስ (መሳሪያዎች) እና የክላውድ ዎርክስፔስ መፍትሄዎችን ለገበያ ማቅረቡን አስታውቋል።

ዘኔክሰስ የተሰኙት ስማርት ዲቫይሶች የሞባይል ስልኮች፣ታብሌቶች፣ ዴስክቶፖች፣ ላፕቶፖች እና የክላውድ ዎርክስፔስ መፍትሔዎችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

ምርቶቹ የዋጋ ተመጣጣኝ ያለመሆን ችግርን ለመፍታት እና የተዘረጋውን ሰፊ የኔትዎርክ መሠረተ ልማት በመጠቀም የዲጂታል ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ያለመ መሆኑን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ዘኔክሰስ ስማርት ስልክ ላይ የሚገኙ ወሳኝ መተግበሪያዎችን በክላውድ አማካይነት በማቅረብ በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ የዲጂታል ተጠቃሚነት ተግዳሮት የሆነውን የዋጋ ውድነት በዘላቂነት በመፍታት የ Digital-First ማኅበረሰቦችን እውን ለማድረግ ያስችላል ብለዋል።

ዘኔክሰስ የኔትወርክ ግንኙነትን፣ የክላውድ አገልግሎቶችንና ምርታማነትን፣ ትምህርትን እና ዕድገትን የሚያፋጥኑ መተግበሪያዎችን በማቅረብ ትምህርትን፣ ግብርናን፣ ጤናን፣ ንግድንና ከዚህም ባሻገር ያሉትን ዘርፎች ያዘምናል ተብሏል።

በኤደን ገብረእግዚአብሔር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review